ራዕይ
ምዕራብ አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በቃሉና በመንፈሱ
የተለወጡና የጽድቅ ተጽዕኖ የሚያመጡ በሳል ደቀመዛሙርት መፍለቂያ ሆና ማየት ( ዮሐ.15፡8 ፤ ማቴ.5፡13–15 ፤28፡18–20)፡፡
ተልዕኮ
ወንጌልን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መስበክ፣ ማስተማር ፣ሁለንተናዊ አገልግሎት
መስጠትና ለጌታ ምጽዓት የተዘጋጁ በሳል ደቀመዛሙርትን ማፍራት ( ማር.16፡15 ፤ማቴ.28፡18–20 ፤5፡13–15 ፤24፡42 ፣44 ፤25፡13 ፤ፊል.3፡20–21፤ቆላ.1፡28)
ዓላማ
- ወንጌልን ለአካባቢያችን ህብረተሰብ በማድረስ
- ያመኑትን በእግዚአብሔር ቃል በማነፅ
- አማኞች በተቀበሉት ስጦታ በማገልግል
- ሁለንተናዊ አገልግሎት በማበርከት
- በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተለወጠ ህይወት ጌታን በማምለክ
እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር ን ማ ክ በ ር ነ ው፡፡
የእገልግሎት ዘርፎች
የትምህርት አገልግሎት ዘርፍ
የልማት አገልግሎት ዘርፍ
የልጆችና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት (ኮንፓሽን)
ጋብቻ እና ቤተሰብ ማማከር ዘርፍ
የወንጌል ስርጭት ዘርፍ
የእረኝነት አገልግሎት ዘርፍ
የልጆች እና ወጣቶች ዘርፍ
የዲያቆን አገልግሎት ዘርፍ
የወንጌል ስርጭት ዘርፍ
ዕሴቶቻችን
እምነት
(ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ስለማቻል) ዕብ.11፡1–39፣ዕብ.11፡6
ቅድስና
(በተቀደሰ ሕይወት መኖር፤(በኑሮ ሁሉ) ያለ ቅድስና እግዚአብሔርን ማየት
ስለማይቻል) 1ኛ.ጴጥ.1፡15–16፤ዕብ.12፡14
ፍቅር
(ለእግዚአብሔር፤ለእርስ በርስ፤ላልዳኑትም የምናሳየው መታወቂያችንም
ስለሆነ) ማር12፡30፤ዮሐ.13፡34–35፤1ኛቆሮ.13፡1–7፤
ይቅርታ
( ልባዊ፣እውነተኛና እግዚአብሔር የሚቀበለው) ማቴ.6፡14፤ማር.11፡25 – 26፤ኤፌ.4፡32
አንድነትን መጠበቅ
(ክርስቶስ በቤዛነት ሞቱ የመሠረተውን የክርስቶስን
ቤተክርስቲያን አንድነት በትጋት መጠበቅ (መዝ.133፡13፤ኤፌ.4፡3፤ ቆላ.3፡15፤ሮሜ.15፡5–6፣የሐ.17፡20–22) ፡፡
ሕብረት
( ክርስቶሳዊ ቤተሰብነትን ለማጠናከር(በህብረት ፀጋ መከፋፈል) ለመፀለይ፤በህብረት ቃሉን ለመማር፤በህብረት ለማገልገል፤ለመተናነጽ፤ ለመተዋወቅ፤ለመደጋገፍ ለመሸካከም፤ጌታን ለማክበር፤)
የሐዋ.2፡42፤ዕብ.10፡24–25
ሎሌ–አገልጋይነት
(ሕያዋን የመሆናችን ማሳያ ነው፡፡ ማንነታችን ነው፡፡ ባለ አደራነታችንን በመገንዘብ ከእግዚአብሔር በተቀበልነው ሥጦታ ሁሉ ቤተክርስቲያንን በማነጽና በማሳደግ እግዚአብሔርን ማክበር) ሮሜ.12፡6–8 ፤1ኛቆሮ.14፡26፤1ኛጴጥ.4፡10–11፤2ኛቆሮ.5፡18
ምስክርነት
ለወንጌል የአምባሳደርነት ኃላፊነታችንን በቃልና በኑሮ በየትኛውም ጊዜና ሥፍራ መወጣት (ማቴ.10፡32–33፣28÷19–20፣የሐዋ.1፡8፣2ኛቆሮ.5፡18–20…አጀንዳ 2819)
ፀሎት
የአባትና የልጆቹ መነጋገሪያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ የልጅነት ሥልጣናችንን/ መብታችንን የምንለማመድበት መንገድ ነው (ዮሐ.1÷12፣ማር.14÷36፣ሮሜ 8÷15፣ገላ.4÷6)፡፡
እግዚአብሔር እኛን ልጆቹን እንድንጸልይ ይፈልጋል፣እንድንጸልይ አዝዞናል፡፡ፀሎት የእኛን አለመቻል፤እግዚአብሔርን ሁሉን መቻል ማመናችንን ማሳያ ነው (ሉቃ.18÷1፣ቆላ.4÷2፣1ተሳ.5÷17፣1ጢሞ.2፡1)
መታዘዝ
ለእግዚአብሔርና በሕይወታችን ላይ ባለሥልጣን ለሆኑት ሁሉ እንደ ቃሉ ታዛዥነታችን
መረጋገጥ አለበት (1ሣሙ.15፡22–23፤1ኛቆሮ. 16÷16፤ኤፌ. 6÷1፤ ቆላ. 3÷18፣20፤ዕብ.
13÷17፤1ጴጥ. 2÷14፣18….)
ፍትሃዊነት/አለማድላት
ሁሉን በእኩል ዐይን ማየት፣በእኩል ማስተናገድ ምክንያቱም
አባታችን አድልዊ አይደለም (ዘጸ.23÷1–3፣6–7፤ዘዳ.1÷16 17፣10÷17፣16÷19–20፤ኢዮ.34÷19፣ሮሜ 2÷11፣ገላ.2÷6፣ኤፌ.6÷9)፡
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሞላት/መጋል
(በምንኖርበት በዚህ ብልሹ ዓለም ውስጥ ለወንጌል እውነት መኖርና ማገልገል የሚቻለው
በመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታና አመራር ብቻ ስለሆነ ነው፡፡)
ዘካ.4፡6፤ሉቃ.24፡49፤የሐዋ.1፡8፤ሮሜ14፡11፤ገላ.5፡16፤22፤ኤፌ.5፡18.
አምልኮ
(በግልና በጋራ ለተገለጠልን አምላካዊ ማንነቱ፤ ወደር ለሌለው ማዳኑ፤ቀጥር ሥፍር
ስለሌለው ውለታው በሁሉም ሥፍራና ጊዜ የምንሰጠውን
ስግደት፤ውዳሴ፤አድናቆት፤ምስጋና፤መታዘዝ፣መገዛት፤አክብሮትና ፍጹም መሰጠትን የሚያመለክት
ምላሽ ነው) መዝ.145፡147፤ዕብ.12፡28፤13፡13 ዮሐ.4፡24
ሁለንተናዊ አገልግሎትን ማበርከት
(ሙሉውን ሰው ማገልገል፤ጩኸታችን እንዲሰማ የሌሎችን ጨኸት መስማት፤በቃልና በተግባር ማምለክ ስላለብን) የሐዋ.24÷1–7፤ገላ.2÷10፤ያዕ.1÷27፡፡
ተግሣጽ
(አንድ ከጌታ መንገድ፣ከጌታ ሥርዓት፣ከጌታ ቃልና ፍቃድ (ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት) የወጣን ወገን፡–በፍቅርና በትህትና ማረም፣ማቅናት ፣መመለስና ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወትን እንደገና እንዲቀጥል ማገዝ/ማስቻል ነው፡፡) ገላ. 6÷1፣2ኛጢሞ.4÷2፣ዕብ.12÷4–11፡፡
የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ ወርቅና ብር ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ !!